ሰላም በአምስት አመቷ የአንደኛ ክፍል ትምህርቷ አጋማሽ ላይ ወደ አዲስ የካቶሊክ ትምህርት ቤት ተዘዋወረች። በዛንም ጊዜ የክፍሎቿ ልጆች ከቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት ጀምሮ አብረው ትምህርታቸውን ይከታተሉ ስለነበር ቀድሞ የተመሰረተ ጓደኝነት ነበራቸው። ስለዚህም ሰላም ከእነሱ ጋር ጓደኝነት መፍጠር ከበዳት።

ሰላም የጓደኛሞቹን ካየች በኋላ ዘና ያሉ እና ጎበዝ ሴት ልጆች ያሉበት ጓደኛማቾች አገኘች፣ ነገር ግን በተቻላት መጠን ብትሞክርም፣ ጓደኛ እንዲያረጓት ማረግ አልቻለችም። ሳምንታት አለፉ፣ እና ብቸኝነትዋ እያደገ ሄደ። በመጨረሻ፣ አንድ ቀን፣ ምሳ ሰአት ላይ ወደ ታላቅ እህቷ  ሄዳ ምን ማድረግ እንዳለባት ጠየቀቻት። 

“እህቴ የሦስተኛ ክፍል ተማሪ ነበረች፣ እና ወደ ሴቶቹ ሄዳ ጓደኛዬ እንዲሆኑ ነገረቻቸው፤ እነሱም ሆኑ። በዚያን ጊዜ የሶስተኛ ክፍል ተማሪዎች ብዙ ኃይል ነበራቸው!” ትላለች ሰላም። 

ዶ/ር ፅዮን ፋሬው በዚያ የጓደኛ ቡድን ውስጥ ካሉ ተማሪዎች አንዷ ነበረች። እሷ፣ ሰላም እና አንድ ሌላ ጓደኛቸው ለቀጣዮቹ አስር አመታት በጣም ፉክክር ባለበት ትምህርት ቤት እየተፈራረቁ ከአንድ እስከ ሶስት ይወጡ ነበር። እንደ ቀኑ እና እንደ አስተማሪው ሁኔታ አንዳንዴ በመምህራን ዘንድ ተወዳጅ ተማሪዎች አንዳንዴ ደሞ ችግር ፈጣሪዎች ይሆኑ ነበር። 

በነዚህ ጓደኞች መካከል ምንም ነገር ሊፈጠር አይችልም። ሌላው ቀርቶ የፅዮን ቤተሰቦች ወደ አሜሪካ ከተዛወሩ በኋላ የነበረው እርቀት እንኳን አለያቸውም። ለስምንት ዓመታት ያህል አልተገናኙም ነበር፣ ነገር ግን ከዛ በኋላ ሰላም ለስራ ልምምድ ወደ ኒው ዮርክ መጣች እና ተገናኙ።

“ካለፈው ምሽት የጀመርነውን  ንግግር እየጨረስን እንደነበር ነው የተሰማኝ።ሌሊቱን ሙሉ እያወራን ከተማዋን ስንጎበኝ ነበር ያደርነው” ስትል ጽዮን ተናግራለች። 

ሰላም ፅዮን ለጓደኝነታቸውን በአንድ ላይ መቆየት ላደረገችው ሁሉ ታመሰግናታለች። “ለሥራዋ እንደምትደክመው ነው ለጓደኞቿ የምትደክመው” ትላለች ።

ይህ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ለመረዳት የፅዮን ስራ ልናገር። በኮሎምቢያ የህክምና ትምህርት ቤት ተባባሪ ፕሮፌሰር፣ በዩኒቨርሲቲው የድንገተኛ ህክምና ዶክተር እና ወደ ትውልድ አገሯ ተደጋጋሚ ጉዞ ማድረግ የሚያስፈልግበት በኢትዮጵያ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አማካሪ በመሆን ትሰራለች። እነዚህ ሁሉ ስራዎች እንዳሉ ሆኘው፣ ሰላም ከሦስት ዓመታት በፊት  ጽዮንን ለአለም አቀፍ ሳማሪታን በአስተዳዳሪዎች ቦርድ አባልነት ማገልገል ትችል እንደሆን ስታዋያት በደስታ ተስማምታለች። 

ፅዮን ስለ ሰላም ስትናገር “ሰላም መሪ እንድትሆን የተፈጠረች ናት። ሁል ጊዜ ብልህ እና ለጓደኞቿ ምሳሌ የምትሆን ናት። እናቷ መሪ ሴት በመሆን አኳያ በእሷ ላይ የገነባችው በራስ መተማመን በደንብ ይታይባታል።” ትላለች።

ዶ/ር ፅዮን ፍሩት እና ዳይሬክተር ሰላም ተረፈ

በሚቀጥለው ሳምንት ከሰላም ጋር በአፍሪካ እንገናኛለን። አለም አቀፍ ሳማሪታን በአፍሪካ የመስፋፋት ልዩ እድል እንዲያገኝ የሰላም አመራር ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል።

ሰላም ባሳለፍነው ሳምንት የተባበሩት መንግስታት የሴቶች ጉዳይ ኮሚሽን አመታዊ ኮንፈረንስ ላይ ለመገኘት በኒውዮርክ ከተማ ነበረች። እናም ከ30 አመታት በፊት እህቷ ካጣመደቻት ጓደኛዋ፣ ከፅዮን ጋር ጥሩ ጊዜ አሳልፋለች። 

ስራችንን ላይ እንደምናረገው ጥረት ያህል በጓደኝነት ላይ ብዙ ጥረት እናድርግ!

ለሥራቸው መልካም ውጤት ስለሚያገኙ፣ ከአንድ፣ ሁለት መሆን ይሻላል

መክብብ 4:9-10

ማይክ ተንቡሽ, የአለም አቀፍ ሳምራዊ ፕሬዝዳንት

ማይክ በትውልድ ከተማው በዲትሮይት፣ ሚቺጋን ከሁለት አስርት ዓመታት መሪነት ማህበራዊ ለውጥ በኋላ በ2018 IntSamን ተቀላቅሏል። እሱ የሚቺጋን የህግ ተመራቂ እና የጆናታን ውጤት፡ ልጆች እና ትምህርት ቤቶች በድህነት ላይ የሚደረገውን ጦርነት እንዲያሸንፉ የመፅሀፍ ደራሲ ነው። እሱና ባለቤቱ ማሪትዛ በወጣትነት የሚቆዩ ሦስት ልጆች አሏቸው።

Training for Life AMHARIC

በእሽቅድምድም ስፍራ የሚሮጡት፥ ሁሉ እንዲሮጡ ነገር ግን አንዱ ብቻ ዋጋውን እንዲቀበል አታውቁምን? እንዲሁም ታገኙ ዘንድ ሩጡ። የሚታገልም ሁሉ በነገር ሁሉ...

Training for Life SPANISH

¿No saben que en una carrera todos los corredores compiten, pero solo uno obtiene el premio?...

For Richer or Poorer AMHARIC

መልካምፍሬን ያወቅኳት ከአራት አመት በፊት የኮሌጅ ተማሪ እያለች ነበር። እናቷ በአዲስ አበባ ቆሬ የቆሻሻ መጣያ ውስጥ ሰራተኛ ስትሆን በተገናኘንበት ወቅት...

A Girl with a Dream Come True AMHARIC

የስኮላርሺፕ ተጠቃሚዎቻችንን እና ቤተሰቦቻቸውን ለመርዳት እና በዋጋ የማይተመን ፈገግታቸውን ለማየት ስለበቃሁ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ። ትምህርታቸውን...