ከሃያ ሁለት ዓመታት በፊት በታክና፣ ፔሩ  ከነበሩ በጎ ፈቃደኞች ጋር የመኖር እና የማገልገል እድል ነበረኝ ፡፡ በቆይታዬም እንግሊዘኛ በማስተማር እና የቅርጫት ኳስ በማሰልጠን አገለግል ነበር። የታክና ከተማ በፓስፊክ የባህር ዳርቻ እና በአለም ደረቃማ ከሆኑ በረሀዎች አንዱ በሆነው በአንዲስ ተራራ መካከል የምትገኝ ናት። እዚያ በነበርኩባቸው ሁለት ዓመታት  ሦስት ጊዜ ብቻ ቢሆንም የዘነበው፣ ተማሪዎቼ፣ ጎረቤቶቼ እና ጓደኞቼ ከረጃጅሞቹ ተራራዎች የሚፈሰውን ውሃ ነበር የሚጠቀሙት። ነዋሪዎቹ ነገ ከነገ ወዲያ የቧንቧ ውሀ ይመጣል እያሉ ቢጠብቁሞ አንዳንዴ ለሳምንት ያህል ሳይመጣ ይቆያል፡፡

ገላ ለመታጠብ፣ ልብስና እቃ ለማጠብ እንዲሁም ቤት ለማፅዳት ምንም ውሃ አልነበረም። በዚህ ሁኔታ ሳምንት ካለፈ በኋላ   የውሃ ቦቴ መኪኖች በየሰፈሩ በሳምንት ሁለት ጊዜ መዘዋወር ጀመሩ፡፡ በዛ ሰዐት ሁሉም ሰው የያዘውን ስራ ሁሉ አቁሞ ባልዲ፣ በርሜል እና ለውሃ ማጠራቀሚያ የሚሆኑ እቃዎችን ሰብስበው ይወጣሉ፡፡ በቆየሁበት ጊዜ ከውሃ ቦቴ መኪኖች ውሃ ሶስት ጊዜ ቀድቻለሁ፡፡ በቴጉሲጋልፓ ሆንዱራስ በሚገኘው የቡን ሳማሪታኖ ማህበረሰብ ተመሳሳይ ሁኔታ ነው ያለው። በሚያሳዝን ሁኔታ, በቆሻሻ መሰብሰቢው አካባቢ ያሉ ሰዎች አማካይ የህይወት ዕድሜ 35 ዓመት ብቻ ነው፡፡

የዚህ ሕይወት ሰጪ ስጦታ ኃይል ሊቆጠር የማይችል ነው – እኛ በኢትዮጵያ ውስጥ ቀድመን አጣጥመናል።

አዳም፣ ኩሩ እና ፈገግታ

በዚህ አመት መጀመሪያ አካባቢ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ የሚገኙ ጓደኞቻችንን የመጎብኘት እድል ነበረኝ። ከሶስት አመታት በፊት፣ ማህበረሰቡ በውሃ ቦቴ መኪኖች ብቻ ነበር የሚጠቀመው። ትንሽ ቆይቶ ግን አንድ ቧንቧ  ተገጠመላቸው ፤ ይሁንና ሁሉም ሰው ከዚች ቧንቧ ስለሚጠቀሞ በጣም አሰልቺ ሰልፍ ነበር። ልጆች ውሃ ለመቅዳት ጥናታቸውን ትተው ተሰልፈው ይጠብቃሉ። አሁን ላይ ግን ማህበረሰቡ በቀላሉ ውሃ ማግኘት በመቻሉ የበለጠ ጤናማ እና ጠንካራ ሆነዋል ፤ የተሻለ አቋም ላይም ይገኛሉ፡፡  በ2021 ከአለም አቀፍ ሳማሪታን ጋር በመተባበር ሁለት የውሃ ጉድጓዶችን ቆፍረናል። ከማህበረሰቡ የተወጣጣ የውሃ አስተዳደር ቦርድ በትንሽ ክፍያ ውሃ ያስሞላል አዲሱንም ሻወር ያስጠቅማል፡፡ በማህበረሰቡ ብዙ የሥጋ ደዌ በሽተኞች  ስለሚገኙ ይህ አገልግሎት የግል ንጽህናቸውን በመጠበቅ ራሳቸውን ከበሽታው መከላከል እንዲችሉ ይረዳቸዋል።

 አዳም የተባለች የውሃ አሰተዳደር ቦርድ አባል ሆና የሻወር እና የውሃ አገልግሎቶችን ለመቆጣጠር የተቀጠረች ሴት አጊኝቼ ነበር። ጀሪካኑን ለመሙላት ሁለት ማይል ከአህያው ጋር ተጉዞ የመጣን ሰው 3 የኢትዮጵያ ብር ታስከፍላለች።  የውሃው ጉድጓድ ለእሷ እና ለማህበረሰቡ በሚሰጠው ጥቅም በጣም ደስተኛ ናት፡፡ በስራዋም ትኮራ ነበር። ይህ አገልግሎት ባይኖር ኖሮ  እና እርሷም እዛ ተቀጥራ ባትሰራ ኖሮ ባለባት የለምፅ በሽታ ምክንያት እጣ ፋንታዋ በጎዳና ላይ መለመን እና በቆሻሻ መጣያ ውስጥ ቆሻሻ መሰብሰብ ይሆን ነበር ። ስለ አዳሞ ሳስብ እየሱስ ከአንዲት ሴት ጋር የውኃ ጉድጓድ ጋር የተገናኘበትን የወንጌል ታሪክ ያስታውሰኛል። ህይወት የምሰጣት መስሎ አልተሰማኝም ፤ ይልቁንም የሷ ለውጥ አስገርሞኛል። ይህች ሴት አሁን አቅም፣ አላማ እና ክብር ያላት ሆናለቾ።

የወጣቶቹ ምንጭ አለ? አዎን፣ እንደ እርስዎ ያሉ ለጋሾች ክርስቶስ በሚወደው መልኩ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ በመቶዎች የሚቆጠሩ ህዝቦች ውሃ እንዲገኙ በማድረግ  ለውጥ እያመጡ ነው። ዛሬ የሰው ልጅ መሰረታዊ  መብት በሆነው በውሃ ዙሪያ በሚከበረው የአለም የውሃ ቀን ለማክበር የውሃው ጉድጓድ ጋር ይቀላቀሉናል?

የቴጉሲጋልፓ የውሃ ግንብ ግንባታ እየተጠናቀቀ ነው።
የውሃ ፕሮጀክቱ በኤፕሪል መጨረሻ ላይ ዝግጁ ይሆናል!

አንድሬው ፓውክ

አንድሪው ከ2007 ጀምሮ ከአለም አቀፍ ሳምራዊ ጋር ሆኖ በአምስት ሀገራት ፕሮግራሞቹን ይከታተላል። ከቅዱስ ዮሐንስ ኢየሱሳ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመርቃ በአለም አቀፍ ጥናት ሁለተኛ ዲግሪዋን አግኝታለች። በአን አርቦር የቅድስት ማርያም ተማሪ አጥቢያን ይማራል፣ ጉጉ የወፍ ተመልካች ነው፣ እና በመለኪያ የወንዶች መዘምራን ይዘምራል።

Training for Life AMHARIC

በእሽቅድምድም ስፍራ የሚሮጡት፥ ሁሉ እንዲሮጡ ነገር ግን አንዱ ብቻ ዋጋውን እንዲቀበል አታውቁምን? እንዲሁም ታገኙ ዘንድ ሩጡ። የሚታገልም ሁሉ በነገር ሁሉ...

Training for Life SPANISH

¿No saben que en una carrera todos los corredores compiten, pero solo uno obtiene el premio?...

For Richer or Poorer AMHARIC

መልካምፍሬን ያወቅኳት ከአራት አመት በፊት የኮሌጅ ተማሪ እያለች ነበር። እናቷ በአዲስ አበባ ቆሬ የቆሻሻ መጣያ ውስጥ ሰራተኛ ስትሆን በተገናኘንበት ወቅት...

A Girl with a Dream Come True AMHARIC

የስኮላርሺፕ ተጠቃሚዎቻችንን እና ቤተሰቦቻቸውን ለመርዳት እና በዋጋ የማይተመን ፈገግታቸውን ለማየት ስለበቃሁ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ። ትምህርታቸውን...