መላልሰው በጠየቁት ጊዜ ግን ቀና ብሎ። ከእናንተ ኃጢአት የሌለበት አስቀድሞ በድንጋይ ይውገራት አላቸው።”

ዩሀንስ 8:7

ስህተት ሰርታችሁ ሁለተኛ እድል ተሰጥተው ያውቃሉ? ይቅርታ ሲጠይቁ ያ እድል ቢከለከልስ?
 
ሁላችንም ቢያንስ ሁለተኛ እድል እንደሚያስፈልገን አንድ ተማሪያችን አነሳልኝ። እኛ ሁል ጊዜ በተሻለ መንገድ ወይም ወላጆቻችን እንድንሰራ እንደሚፈልጉት አንሰራም ፣ ግን ሁለተኛ እድሎች የበለጠ ጠንካራ ሆነን እንድንገኝ እድሉን ይሰጡናል።

ኢርማ 18 ዓመቷ ሲሆን ነፍሰ ጡር የሆነች  የፕሮግራማችን ተጠቃሚ ናት። እናቷ ስለ እርግዝናዋ ስትነግረኝ በጣም አዝኛለሁ፣ ቅር ተሰኝቻለሁ፣ በዛም ላይ ተናደድኩ። ማመን አቃተኝ! ኢንተርናሽናል ሳማሪታን በትምህርት ቤት እንድትቆይ ሁሉንም ነገር ሰጥቷት ነበር፣ ነገር ግን ፖሊሲያችን እርግዝና ከስኮላርሺፕ ፕሮግራም ለመባረር ምክንያት ነው። ኢርማ ይህን ታውቅ ነበር። ትምህርቷን እንዴት እንዲህ አደጋ ላይ ልትጥል ቻለች? ያለ ስኮላርሺፕ እርዳታ ይቅርና በእርዳታው ራሱ በትምህርት ቤት መቆየት ለእናት ከባድ ነው!
 
እናቷ ስለዚህ ሁኔታ በተደባለቀ ስሜት ነገረችኝ። በአንድ በኩል እናት ልጆቿ መጀመሪያ ሲማሩ፣ ሲመረቁ፣ ሲጋቡ እና በመጨረሻም ልጆች ያሉበት ቤተሰብ ሲመሰርቱ ሁልጊዜ ስለምታስብ አዝናለች። በሌላ በኩል ግን የልጅ ልጅ በማግኘቷ ደስተኛ ነበረች። ልጅ በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ሁል ጊዜ የእግዚአብሔር በረከት ይሆናል።
 
እርዳታ ለማግኘት ወደ ኢንተርናሽናል ሳማሪታን ቡድን ዞርኩ። አንድ ላይ፣ ሙሉ ስኮላርሺፕ ባይሆንም ለኢርማ የተወሰነ ደረጃ ድጋፍ ለማድረግ ወሰንን። የስራ ባልደረቦቼም ይቅር ባይ እንድሆን መከሩኝ። እነሱም “ሮኒያ፣ ለዚች ልጅ እና ለልጇ የተሻለ ህይወት እንዲኖራቸው የምንረዳበትን  እድል እንፈልግ” አሉኝ። ስለዚህ ለራሴ፣ “ተልዕኮዬ ሁል ጊዜ መፍትሄዎችን ወይም ለሚፈልጉት አዲስ እድሎችን መፈለግ ስለሆነ ለምን ተናደድኩ?” ብዬ ራሴን ጠየኩ። እሷ እና ልጇ ያ ብሩህ የወደፊት ጊዜ እንዲኖራቸው ትኩረቴን ኢርማንን ይቅር ወደማለት እና ወደ መርዳት አዞርኩ።
 
ኢርማ ይቅርታ ጠየቀች እና ትምህርቷን ለመጨረስ ቆርጣ ነበር። በአይነ መረብ ላይ ትምህርቷን እንድትቀጥል የሚያስችል እቅድ ፈጠርን። የኢርማ እናት ብትናደድም በትምህርት ቤት የመቆየት እቅዷን ሙሉ በሙሉ ትደግፋለች፣ ኢርማ በምትማርበት ጊዜ ልጇን ለመንከባከብ ፈቃደኛ ነች እና ሴት ልጇን በእርግዝናዋ ሁሉ በፍቅር እና በጸጋ ደግፋለች።

እርስዎ እንደ ለጋሽ፣ እንደ ቡድን ጓደኛ ወይም በጎ ፈቃደኞች፣ እንዲሁም የኢንተርናሽናል ሳማሪታን አካል በመሆን ኢርማን ለመደገፍ ትረዳላቹ። አንድ ላይ ሆነን ያልተጠበቁ ሁኔታዎች ቢያጋጥሟትም ትምህርቷን እንድትቀጥል እድሉን ሰጥተናል እና ያደረግነው ጥሩ ነገር ነው! ኢርማ ከእርግዝናዋ በፊት ከነበራት በበለጠ ተነሳሽነት ትምህርቷን ቀጥላለች። እሷም “እኔ ተመርቄ ሁሉም በእኔ ስኬት እንዲኮሩ አደርጋለሁ” አለችን።
 
ሁሉም ሰው በተለይ ህፃናት ያልተጠበቁ ውጤቶች ያሏቸውን ስህተቶች  ይሠራሉ፣ ነገር ግን ሰዎች ትንሽ በመረዳት እና በይቅርታ ማግኘት የሚችሉት ነገር በእውነት አስደናቂ ነው። ኢርማ በተሰጣት ሁለተኛ እድል ባደረገችው ነገር ሁሉ ኩራት ይሰማኛል። ወደፊት የምትሆነውን  ሴት፣ እናት እና ሳማሪታን ለማየት እጓጓለሁ።

በዚህ ሳምንት ነጸብራቅ ላይ በተወያየነው ስሜት ቀስቃሽ ይዘት ምክንያት የጸሐፊውን ስም፣ የትውልድ ሀገር እና የታሪኩን ስም በመቀየር የተጠቀሱት ግለሰቦች በቀላሉ የማይታወቁ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ወስነናል።

Does the Fountain of Youth Exist? AMHARIC

ከሃያ ሁለት ዓመታት በፊት በታክና፣ ፔሩ  ከነበሩ በጎ ፈቃደኞች ጋር የመኖር እና የማገልገል እድል ነበረኝ ፡፡ በቆይታዬም እንግሊዘኛ በማስተማር እና...

A Sister Can Make All the Difference AMHARIC

ሰላም በአምስት አመቷ የአንደኛ ክፍል ትምህርቷ አጋማሽ ላይ ወደ አዲስ የካቶሊክ ትምህርት ቤት ተዘዋወረች። በዛንም ጊዜ የክፍሎቿ ልጆች ከቅድመ መደበኛ...

A Second Chance SPANISH

“Pero como insistían en preguntarle, Jesús se enderezó y les dijo: 'El que de vosotros esté sin...

We Need Your Prayers AMHARIC

  ሐሙስ ዕለት ወደ ዋሽንግተን ዲሲ በአውሮፕላን እየተሳፈርኩ ሳለ ከቡድናችን መሪዎች አንዱ አስደንጋጭ የስልክ ጥሪ ደረሰኝ። “ፍሬዲ” እና ስድስት...