በቤትዎ ፣ በቢሮዎ ፣ በሆቴልዎ ፣ በአከባቢዎ ውስጥ ውሃ  ለአንድ ቀን ባይኖር ብለው አስበው ያቃሉ? ባይኖር እንጼት እንደሚኖሩ መገመት ይችላሉ? ለአንድ ቀን ችግር የለውም በሕይወት መኖር ይችላሉ ፣ ነገር ግን በየቀኑ ውሃ ካላገኙስ? ወይም በወር ሁለት ጊዜ ብቻ ቢሆንስ? ከየውሃ ጭነት መኪናዎች በመግዛትና መተዳደር ይችላሉ፡፡ በወር ሁለት ጊዜ ብቻ ካገኙ ፣ መቆጠብን ይማራሉ፡፡  ነገር ግን እሱን ለመግዛት ገንዘብ ከሌለዎት እና በወር ሁለት ጊዜ የማያገኙ ከሆነ ምን ይከሰታል?

በቡኤን ሳማሪታኖ ማህበረሰብ ውስጥ የሚኖሩት ሰዎች ሁኔታ ይህ ነው፡፡ ይህ ማህበረሰብ 2,800 ወንዶች ፣ ልጃገረዶች ፣ ወጣቶች ፣ እንዲሁም አዋቂዎችን የያዘ ሲሆን  የሚተዳደሩት ቆሻሻ በመሰባሰብ  እና በመሸጥ ነው፡፡ ወደ 4,000 ሌምፒራስ ( $ 162 ዶላር ) በወር ገቢ ያገኛሉ፡፡ በእነዚያ 4,000 ሌምፒራስ አማካኝነት አንድ ሠው  ስድስት ሰዎች መመገብ ፣ ለኤሌክትሪክ ፣ ለልብስ ፣ ለቤት እቃዎች ፣ ጫማ እና ውሃ መግዛት አለበት፡፡ በግልጽ ለማየት እንደሚቻለው ይህ በቂ ውሃ አይሆንም ፣ ለዚም ሰዎች የዝናብ ውሃን ምግብ ለማብሰል ፣ ለመታጠብ ፣ ቤት ለማፅዳት እና ከሁሉም በላይ ለመጠጥ ውሃ ለመጠቀም ወስነዋል.

ዓለም አቀፍ ሳምራታን ይህንን ማህበረሰብ በደረጃ በደረጃ መርሃግብር በኩል ይደግፋል ፣ እኔም እምሰራው እዚ ላይ ነው፡፡ ስሜ ሮኒያ ይባላል፡፡ እናም ለአምስት ዓመታት ለአለም አቀፍ ሳምራታን እየሰራሁ ነው፡፡ ስራዬ ከስኮላርሺፕ ተጠቃሚዎች እና ከቤተሰቦቻቸው ጋር አብሮ መጓዝ እና በሚፈልጉት ሁሉ መደገፍ ነው፡፡ ያለምንም ጥርጥር ውሃ የዚህ ማህበረሰብ በጣም አጣዳፊ ፍላጎቶች አንዱ ነው፡፡ አንድ ቀን ከስኮላርሺፕ ተጠቃሚዎች አንዱ በሆነው በሚላግሮስ ቤት ውስጥ የቤት ጉብኝት እያደረግሁ ነበር ፣ እናም ስለ የውሃ ምንጮቻቸው ሙሉ በሙሉ ረሳሁ፡፡ ሁለት ጊዜ ሳላስብ አንድ ብርጭቆ ውሃ ሊሰጡኝ ይችሉ እንደሆነ ጠየኩ፡፡ ባስታወስኩ ጊዜ ውሃውን ሰተውኝ ነበር፣ እናም ቤተሰቡ መጥፎ ስሜት እንዳይሰማው ብዬ  ሁለት ጉንጭ ጠጣሁ፡፡ የምታመም  መስሎኝ ነበር ፣ ግን እግዚአብሔርን ይመስገን ምንም ነገር አልሆንኩም፡፡  እነዚህ ቤተሰቦች ንጹህ የውሃ ስርዓት እንደሚያስፈልጋቸው ተገነዘብኩ፡፡

ሮኒያ በገና ላይ ከሚላግሮስ ቤተሰብ ጋር

ከዚያም የዓለም አቀፍ ሳምራታን  ፕሬዝዳንት ማይክ ቴንበስች እንዲደግፉልን ጠየቅሁ፡፡ እሱ ብዙ ገንዘብ ነው አለ ፣ ግን ሙከራ አላቆምኩም፡፡ ከማይክ ጋር  ውይይት ቀጠልኩ ፣ እና ማይክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ፕሮጀክቱን ያፀድቃል ብሎ ተስፋ በማድረግ ወደ እግዚአብሔር መፀለይ ቀጠለ እናም በመጨረሻ ተሳካ፡፡ በዚህም እጅግ ደስተኛ ሆንኩ፡፡ እውነት ሆነ፡፡ ቡኤን ሳማሪታኖ ውሃ ሊኖረው ነው፡፡. ቀላል ይመስላል  ግን እግዚአብሔር ብዙ ሰዎችን እንደ ተማሪዎች ፣ አስተማሪዎች ፣ አባቶች ፣ እናቶች ፣ የንግድ ባለሙያዎች ፣ አብያተ ክርስቲያናት ፣ ፓስተሮች, ፈቃደኛ ሠራተኞች ፣ ዓለም አቀፍ ጓደኞች እና ዓለም አቀፍ ቡድኖች ሁሉ ለለውጥ የሚጠቀምበት ፕሮጀክት ሆኖ ቀጥሏል፡፡ ስለደገፉን ለጋሾች ሁሉ ምን ማለት እችላለሁ? በዚህ ተልእኮ ላይ ለምን እንዳስቀመጣቸው እግዚአብሔር ያውቃል፡፡

የፕሮጀክቱን እድገት እና የብዙ ቤተሰቦች ደስታ በውሃ ዝርጋታው በማየቴ በጣም ደስተኛ ነኝ፡፡ እውን የሆነ ህልም ስለሆነ ብዙዎች  ማመን አይችሉም፡፡  የሚላግሮስ እናት በደስታ እንባ ውስጥ ሆና የውሃ ማማዋን እና የውሃ ማጠራቀሚያዋን ጨምሮ የውሃ መስመሩ እንዴት እንደሚሰራ አሳየችን ፡፡ ብዙም ሳይቆይ የተፈጥሮ ማጣሪያም ይኖራታል፡፡  በዚህ መልኩ የሁሉም  ተጠቃሚዎች ቤተሰቦች እና ማህበረሰቡ ውሃ  ያገኛሉ  ፣ እና ውሃ ብቻ ሳይሆን ንጹህ ውሃ፡፡  ሁላችሁንም ስለ ድጋፍዎ እናመሰግናለን ፣ ህይወትን ስለለወጡ እናመሰግናለን ፣ እናም በጣም የሚያስከፉ የኑሮ ሁኔታዎችን በማሻሻልዎ እናመሰግናለን.፡፡ እኔ ስለ ድጋፍዎ ሁሉ ለማመስገን እነዚህን ቃላት እጽፋለሁ፡፡  ድርሻዎትን ላበረከቱ ሁሉ እግዚአብሔር ምስጋና ዬን ያውቃል፡፡ በቡኤን ሳማሪታኖ ማህበረሰብ ውስጥ ባልኖርም ፣ ግን እኔ የዚህ አካል እንደሆንኩ ይሰማኛል፡፡ ለእግዚአብሔርን ብዙ ምስጋና እንሰጣለን፡፡

የውሃ ፕሮጀክቱ እንዴት ይሠራል? ለመላው ማህበረሰብ የሚሆነው ዋናው ቧንቧ እንዲሁም ለእያንዳንዱ ቤት  የሚሆኑ የውሃ ቧንቧዎች እየተዘረጉ ነው፡፡ እንዲሁም  ለዋናው የውሃ ማጠራቀሚያ  ለማስቀመጫ ማማ  እና በአንድ ቤተሰብ ውስጥ አንድ የውሃ ማጠራቀሚያ እየተገጠመ ነው፡፡ ለመላው ማህበረሰብ እንዲሰራጭ 10,000 ጋሎን አቅም ያለው የውሃታንከር እየተገነባ ነው፡፡ ይህ ታንከር ለእያንዳንዱ ቤተሰብ በሳምንት ሁለት ጊዜ ውሃ መስጠት እና ለእያንዳንዱ ቤተሰብ የተፈጥሮ ማጣሪያ ይሰጣል፡፡ እነዚህ ቤተሰቦች ንጹህ ውሃ ዋስትና እንዲሰጥ ታንከሮቻቸውን ስለማጠብ ሥልጠና እና ምክር ያገኛሉ፡፡

የመሬት ውስጥ ቧንቧዎች ፍንጮች

የማህበረሰብ የውሃ ግንብ መገንባት

የተጠናቀቀ የቤት ውስጥ የውሃ ማጠራቀሚያ

ሮኒያ, የፕሮግራም ዳይሬክተር

ሮኒያ በእንግሊዘኛ ትኩረት በመስጠት በውጭ ቋንቋዎች የመጀመሪያ ዲግሪ አላት። ለብዙ አመታት ሮኒያ በቴጉሲጋልፓ ማዘጋጃ ቤት ቆሻሻ መጣያ ውስጥ ለሚሰሩ ልጆች፣ ጎረምሶች እና ጎልማሶች እድሎችን ለማስፋት እራሷን ሰጥታለች።

Does the Fountain of Youth Exist? AMHARIC

ከሃያ ሁለት ዓመታት በፊት በታክና፣ ፔሩ  ከነበሩ በጎ ፈቃደኞች ጋር የመኖር እና የማገልገል እድል ነበረኝ ፡፡ በቆይታዬም እንግሊዘኛ በማስተማር እና...

A Sister Can Make All the Difference AMHARIC

ሰላም በአምስት አመቷ የአንደኛ ክፍል ትምህርቷ አጋማሽ ላይ ወደ አዲስ የካቶሊክ ትምህርት ቤት ተዘዋወረች። በዛንም ጊዜ የክፍሎቿ ልጆች ከቅድመ መደበኛ...

A Second Chance AMHARIC

"መላልሰው በጠየቁት ጊዜ ግን ቀና ብሎ። ከእናንተ ኃጢአት የሌለበት አስቀድሞ በድንጋይ ይውገራት አላቸው።" ዩሀንስ 8:7ስህተት ሰርታችሁ ሁለተኛ እድል...

A Second Chance SPANISH

“Pero como insistían en preguntarle, Jesús se enderezó y les dijo: 'El que de vosotros esté sin...