መልካምፍሬን ያወቅኳት ከአራት አመት በፊት የኮሌጅ ተማሪ እያለች ነበር። እናቷ በአዲስ አበባ ቆሬ የቆሻሻ መጣያ ውስጥ ሰራተኛ ስትሆን በተገናኘንበት ወቅት በሳንባ ህመም ምክንያት እናቷ በቆሻሻ መጣያ ቦታ መስራት መቀጠል አልቻለችም፡፡ እናቷ የልጇን የትምህርት ወጪ ለመሸፈን መንገድ ዳር ምግብ መስራት እና በአቅራቢያው በሚገኝ መጠጥ ቤት መክሰስ መሸጥ ጀመረች። መልካም የምታገኘውን ማንኛውንም ሥራ መሥራት ነበረባት ምክንያቱም ምንም እንኳን እናቷ ብትሰራም የምታገኘው ገቢ በቂ አልነበረም። ይሁንና መልካም እና እናቷ ጠንካራ እና ፅኑ ነበሩ። በመጨረሻም መልካም በአለም አቀፍ ሳምሪታን በኩል የነፃ ትምህርት ዕድል አግኝታ ትምህርቷ ላይ ትኩረት ማድረግ ቻለች። በማኔጅመንት ዲግሪ በሜዳሊያ ተመርቃ አሁን በአዲስ አበባ ከተማ መንገድ ባለስልጣን በአስተዳዳሪነት ትሰራለች።

“ከእግዚአብሔር ቀጥሎ” ትላለች መልካም፣ “ለአለም አቀፍ ሳምሪታን እርዳታ እና ለእናቴ ምስጋናዬን አቀርባለሁ ።”

የአለም አቀፍ ሳምሪታን ተማሪዎች ከሁለት ሳምንት በፊት ስለ ቅዳሜና እሁድ እቅዶቼ ሲጠይቁኝ ደስታ ተሰማኝ። እኔም “ ምን አስባቹ ነው?” ብዬ መለስኩላቸው። መልካምም በአዲስ አበባ የሚኖሩ ጥሩ ቤተሰብ ካለው መልካም ከሆነ ሰው ጋር ቀለበት ማሰሯን ገለፀችልኝ። ለእኔ እና ለእንግዳወርቅ ለማ በአዲሱ ቤታቸው የሚደረገውን አማቾቿ ያዘጋጁትን ልዩ የሰርግ ዝግጅት እንድንቀላቀል ግብዣ አቀረበችልን። በጣም ተደስቼ  የእንደዚህ አይነት መልካም ቀን አካል መሆኔ በጣም እንደሚያስደስተኝ ነገርኳት።

እኔና እንግዳ ቅዳሜ እኩለ ቀን ላይ የምልካም ቤት ደረስን እና በሚያምር ሁኔታ ባጌጡ መኪኖች እና በአበባ ባጌጠ መንገድ ገባን። እናቷ በደስታ ተቀበለችን። መልካም በጣም ደስተኛ ነበረች ፣ ቆዳዋ ያበራል ፣ መጀመሪያ ከተገናኘንበት ጊዜ የበለጠ ወጣትነት ይታይባታል።

ሁለቱ የቀድሞ የአለም አቀፍ ሳምሪታን ተማሪዎች የሆኑት የሙሽሪት ሚዜዎች ከፊት ለፊታችን ተቀምጠዋል። ስለመልካም ኑሮ እያሰብኩ ሳለ ሙሽሮቹ በድምቀት ተጨብጭቦላቸው ገቡ። መልካም የባህል ልብሷን እና ካባዋን ለብሳ በግርማ ሞገስ ገባች ። መልካም የጥንካሬ እና የጽናት  ምሳሌ ነች።

ተጋባዥ እንግዳው ሁሉ ለአዲስ ተጋቢዎቹ ስጦታ አበረከቱ መረቋቸውም። በሥነ ሥርዓቱ ወቅት ሙሽሪት እና ሙሽራው ደስተኛ ሆነው እያወሩ እና እየሳቁ አሳለፉ፤ ትዳራቸው የተባረከ እንደሆነ ያስታውቃል ።

እርስ በእርሳቸው መሐላ ገብተው በበጎና በክፉ፣ በሀብትና በድህነት ፣ በበሽታና በጤንነት አብረው እንደሚሆኑ ቃል ተገባቡ። አንድም ሆኑ። እንግዶቹን ተሰናብተው የጋራ ሕይወታቸውን ለመጀመር ሲወጡ የማቴዎስ ወንጌል 19፡6 ጥቅስ ወደ አይምሮዬ መጣ።

“እንግዲህ አንድ ሥጋ እንጂ ሁለት አይደሉም፤ እንግዲህ እግዚአብሔር ያጣመረውን ማንም አይለየው።”

እኔም ፈገግ አልኩና በልቤ “አሜን አሜን” አልኩ።

መልካም እና ታመነ ግዛው ጥር 29 ቀን 2023 ተጋቡ

ሰላማዊት ተረፈ፣ ዳይሬክተር (ኢትዮጵያ)

 

ሰላም ከኪንግ ኮሌጅ በሶሺዮሎጂ የማስተርስ ዲግሪ ያላት ሲሆን እንዲሁም ህግን፣ አስተዳደርን እና የሴቶችን መብት ተምራለች። የእሷ ጥናት በምስራቅ አፍሪካ በሴቶች ጉዳይ ላይ ከተባበሩት መንግስታት ጋር እንድትሰራ መርቷታል። ፍላጎቷ ማንበብ ነው፣ስለዚህ በኢትዮጵያውያን ደራሲያን የተፃፉ መጽሃፎችን የሚወያይበት የመፅሃፍ ክበብ አዘጋጅታለች።

Does the Fountain of Youth Exist? AMHARIC

ከሃያ ሁለት ዓመታት በፊት በታክና፣ ፔሩ  ከነበሩ በጎ ፈቃደኞች ጋር የመኖር እና የማገልገል እድል ነበረኝ ፡፡ በቆይታዬም እንግሊዘኛ በማስተማር እና...

A Sister Can Make All the Difference AMHARIC

ሰላም በአምስት አመቷ የአንደኛ ክፍል ትምህርቷ አጋማሽ ላይ ወደ አዲስ የካቶሊክ ትምህርት ቤት ተዘዋወረች። በዛንም ጊዜ የክፍሎቿ ልጆች ከቅድመ መደበኛ...

A Second Chance AMHARIC

"መላልሰው በጠየቁት ጊዜ ግን ቀና ብሎ። ከእናንተ ኃጢአት የሌለበት አስቀድሞ በድንጋይ ይውገራት አላቸው።" ዩሀንስ 8:7ስህተት ሰርታችሁ ሁለተኛ እድል...

A Second Chance SPANISH

“Pero como insistían en preguntarle, Jesús se enderezó y les dijo: 'El que de vosotros esté sin...